Sale

ቅኔ: ፍልስፍና ዘጦቢያ (Amharic Edition)

Amazon Digital Services LLC - Kdp
SKU:
9789994474585
|
ISBN13:
9789994474585
$25.00 $24.99
(No reviews yet)
Usually Ships in 24hrs
Current Stock:
Estimated Delivery by: | Fastest delivery by:
Adding to cart… The item has been added
Buy ebook
ፍልስፍና ብዙዎች ሱሰኛ የኾኑበት የዓለማችን የዕውቀት የቸዝ ጨዋታ ነው፡፡ ይኽንንም የቸዝ ጥበብ ባለምጡቅ አእምሮ ፈላስፎች ሠርተውታል/ፈጥረውታል፡፡ ጨዋታውም በአመክንዮ ተጠየቅ (Logic) እንዲካሔድ ተደርጎ ተቀርጽዋል፡፡ የፍልስፍና ምሁራኑም የቀድሞ ሠሪዎቹን በማድነቅና በማዳነቅ ወይም በመተቸት እየተጫወቱት ኖረዋል/ይኖራሉ፡፡ በጨዋታው ንግሥቷን እውነት ለማግኘትም የማሰብ አቅማቸውን (ዕውቀታቸውን) ኹሉ ተጠቅመው ሲወዳደሩ (ሲከራከሩ) ጊዜያቸውን ይፈጃሉ፡፡ ይኽም ጨዋታ የሚካሔደው በቋንቋ ነው፡፡ ኾኖም ብዙዎቹ ምሁራን በቋንቋ አጠቃቀም ስልት የጨዋታውን ውስብስብነት በመጨመር ያልሠለጠነ ሰው (የፍልስፍና ትምህርት ያልተማረ) የማይደርስበት ክልል ሠርተው አስቀምጠውታል፡፡ እነሱ ግን አጨዋወቱን በመሠልጠንና በማሠልጠን ይለማመዱና የመባልን ይወስዳሉ፡፡ ስለኾነም ማዕረጋቸውንና የሠለጠኑበትን ክልል ለማስጠበቅ የጨዋታውን ሜዳ በሥነ አመክንዮ አጥር ስላጠሩት ማን ደፍሮ ይግባበት?...... በቸዝ ጨዋታ ሥልጠና የተጠመዱ ብዙዎቹ አካዳሚዊ የፍልስፍና ምሁራንም ሥልጠናውን የወሰዱት ፍልስፍና በተሠራበት በምክንያት ዘይቤ ብቻ ስለኾነ ፍልስፍና ቅኔነት የሌለው ጥበብ ይመስላቸዋል፡፡ ነገር ግን ምሁራኑን የሥልጠና ተፅእኖ ይዟቸው እንጂ የፍልስፍና ጥበብ የሚገኘው በቅኔነት ተቃኝቶ መኾኑ እርግጥ ነው፡፡ ችግሩ ግን በቸዝ ጨዋታ የማመክነይ (የምክንያታዊነት) ሕግ ብቻ መሸበብና ቅኔነትን ከዐለማወቅ የሚመነጭ መኾኑ ላስተዋለው ሰው ግልጽ ይኾንለታል። ፍልስፍና በተፈጥሮው ቅኔነት ባይኖረው ኖሮም ተራ ጥበብ ኾኖ ይቀር ነበር፡፡ ማመክነይ ብቻ እንጂ መደነቅ የፍልስፍና መሠረት መኾን አይችልም ነበር፡፡ ይኽንን ለመረዳት ምናልባት የፍልስፍናን መሠረታዊ ዕሳቤዎች ከቅኔነት ተፈጥሮ ጋር በማነጻጸር ማየት ይጠይቅ ይኾናል፡፡ለምሳሌ የፍልስፍና ጥበብ


  • | Author: ካሣሁ Kassahun Alemu
  • | Publisher: Amazon Digital Services LLC - Kdp
  • | Publication Date: Apr 07, 2022
  • | Number of Pages: 336 pages
  • | Binding: Paperback or Softback
  • | ISBN-10: 9994474588
  • | ISBN-13: 9789994474585
Author:
Publisher:
Amazon Digital Services LLC - Kdp
Publication Date:
Apr 07, 2022
Number of pages:
336 pages
Binding:
Paperback or Softback
ISBN-10:
9994474588
ISBN-13:
9789994474585